ፕሮጀክቱ ኢነርጂ ማመንጨት ብቻ ሳይሆን ማስተማሪያም ጭምር መሆኑ ተገለጸ።

ፕሮጀክቱ ኢነርጂ ማመንጨት ብቻ ሳይሆን ማስተማሪያም ጭምር መሆኑ ተገለጸ። ሰኔ 06/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከአለምአቀፍ ሶላር አልያንስ (ISA) ጋር በመተባበር በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ግቢ ውስጥ ያስገነባው እና 100 ኪሎዋት የሚያመነጨው የሶላር ኢነርጂ ፕሮጀክት ሀይል ማመንጨት ብቻ ሳይሆን ማስተማሪያም ጭምር መሆኑን ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ ገልጸዋል። ፕሮጀክቱ በይፋ ስራ በጀመረበት እለት ከሚዲያ ጋር ቆይታ ያደረጉት በውሃ ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ ሶላር ሚኒ ግሪዶችን በጣም ገጠርማ ለሆኑ አካባቢዎችና ለተለያዩ ተቋማት ከዚህ በፊት ስንጠቀምበት ቆይተናል ብለዋል። ሶላር ማቀዝቀዣዎችን እና ሶላር መስኖ ፖምፖችን በተለያዩ ክልሎች ለህብረት ስራ ማህበራት ጥቅም ላይ እንዲውሉ በማድረግ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። የተገነባው የሶላር ፕሮጀክት ተቋሙ መጠቀም በሚፈልግበት ሰዓት አገለሰግሎት እየሰጠ ቀሪው ቀጥታ ወደ ዋናው ኤሌክትሪክ መስመር ይገባልም ብለዋል። ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አያይዘውም የሶላር ኢነርጂ አዋጭ ፣ ከብክነትና ብክለት የጸዳ ቴክኖሎጂ በመሆኑ ተሞክሮው በውሃና ኢነርጂ ብቻ የሚቆም ሳይሆን ሌሎች ተቋማትም በተሞክሮ ሊወስዱት የማዚገባ ነው ብለዋል። በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢንተርናሽናል ሶላር አልያንስ ተወካይ አቶ አብይ ግርማ በበኩላቸው የሚመረተው ኃይል ወደ ዋናው የሀይል መስመር ስለሚገባ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሰጠን ስማርት ግሪድ አንድ ላይ በመሆን ጫና ሲኖር ወደ ተቋሙ ይሄዳል እረፍት ቀናት ወደዋናው የሀይል መስመር ሳይባክን ይገባል ብለዋል። አክለውም የገባውንና የወጣውንም ሀይል በሰዓት ምን ያህል ኪሎዋት እንደሆነ ያመለክታል፤ አቅም ያላቸው ባለሃብቶች ይሄንን ቴክኖሎጂ ቢጠቀሙ የሚተርፋቸውን ሀይል ወደግሪድ መስጠት አንደሚችሉም ጠቁመዋል። ቴክኖሎጂው ለሌሎቸ ፕሮጀክቶች ሞዴል ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን በታሪፍ ጭማሪ ምክንያት እየጨመረ የመጣውን የሸማች የሀይል ፍላጎት ውስንነትን ለመፍታትና የኢትዮጵያ የሶላር ኢነርጂ ስትራቴጂ በመቅረፅ የኢነርጂ ደህንነትን ለማሳደግ ያለመ ነው። የግንባታ ስራውን አራራት ኮነስትራክሽን ማከናወኑ ተገልጿል

Share this Post