የአየር ሁኔታ ትንበያ በቀጠናው ሀገራት የድርቅና ጎርፍ ተጋላጭነትን ለመከላከል ጠቃሚ ነው ተባለ፡፡

የአየር ሁኔታ ትንበያ በቀጠናው ሀገራት የድርቅና ጎርፍ ተጋላጭነትን ለመከላከል ጠቃሚ ነው ተባለ፡፡ ግንቦት 12/2017 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ.) የኢጋድ አባል ሀገራት ተወካዮች በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጉብኘት ባደረጉበት ወቅት የሶስት ወራት የአየር ሁኔታ ትንበያ በኢጋድ አባል ሀገራት የሚከሰቱ የድርቅና ጎርፍ ተጋላጭነትን ለመከላከል አይነተኛ መሳሪያ ነው ተብሏል፡፡ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ከኢጋድ አባል ሀገራት ተወካዮች ጋር በነበራቸው ቆይታ በቀጣይ በቀጠናው ሊያጋጥም የሚችል የድርቅና የጎርፍ አደጋን ለመከላከል መንግስታት ከቀረበው የሶስት ወር የቀጠናው የአየር ሁኔታ ትንበያ መነሻ አድርገው በመውስድ መፍትሄዎች ለማስቀመጥ እንደሚረዳቸው ተናግረዋል፡፡ በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘው የአየር ሁኔታ ትንበያ መድረክ የኢትዮጵያ የሜትሮሎጂ እና የውሃ ሀብት መረጃ አደረጃጀት፣ ትንተና እና አጠቃቀም ላይ አባል ሀገራት ተሞክሮ እንደሚያገኙበት ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ኢትዮጵያ የአየር ሁኔታ መረጃ የመሰብሰብ፣ የማደራጀት እና የመተንተን አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መሄዱንና በአሁኑ ወቅት ከ60 በመቶ በላይ የአየር ሁኔታ መከታተያ ጣቢያዎች ዘመናዊ የሆኑ አዉቶማቲክ መሳሪያዎችን መጠቀም መቻሉ ተገጿል፡፡ የኢጋድ አባል ሀገራት ተወካዮች የውሃና ኢነርጂ ዲጂታል ኤግዚቢሽንና የዲጂታል ላይብራሪን ጎብኝተዋል፡፡

Share this Post