የኢትዮጵያ ሶላር ኢነርጂ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን በሀይል ዘርፉ ከሚሳተፉ አካላት ጋር ተወያየ፡፡

የኢትዮጵያ ሶላር ኢነርጂ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን በሀይል ዘርፉ ከሚሳተፉ አካላት ጋር ተወያየ፡፡

ሚያዚያ/2016ዓ.ም(ው.ኢ.ሚ) የኢትዮጵያ ሶላር ኢነርጂ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን በሀይል ዘርፉ ከሚሳተፉ አካላት ጋር ተወያየ፡፡

በፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጅ ዘርፍ አማካሪ አቶ ጎሳየ መንግስቴ ኢትዮጵያ እምቅ የታዳሽ ሀይል ባለቤት ብትሆንም ወደ ግማሽ የሚጠጋ የህብረተሰብ ክፍል በመብራት እጥረት ውስጥ ይገኛል ብለዋል፡፡ እንደ አማካሪው ገለጻ ይህንን የህብረተሰብ ክፍል የመብራት አገልሎት ተጠቃሚ ለማድረግ መንግስት የኤሌክሪፊኬሽን ፕሮግራምን ቀርጾ አስከ 2030 የግሪድ እና ከግሪድ ውጭ የሆኑ ሁሉንም የኢትዮጵያ ህዝብ ወጪ ቆጣቢና የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገቡ የቴክኖሎጂ አማራጮችን በመጠቀም እና ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ የህብረተሰብ ክፍልና ማህበራዊ ተቋማትን በመለየት ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

አክለውም ፕሮግራሙ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት፣ የልማት አጋሮች እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን የጋራ ቁርጠኝነት የሚጠይቅ ትልቅ ጥረት ያስፈልገዋልም ብለዋል።

አማካሪው እንደሚሉት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የግሉ ሴክተር በተለይም የኢትዮጵያ ሶላር ኢነርጂ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን (ESEDA) ፕሮግራሙን ወደ ፊት ለማራመድ ያለውን ወሳኝ ሚና እንደሚገነዘብ ጠቅሰው የተሻሻለው የናሽናል ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም (NEP) በተለይ በግል ኩባንያዎች የሚመራውን ከግሪድ ውጪ ያለውን የህረተሰብ ክፍል የኤሌክትሪክ አገልግሎቱን ተጠቃሚ የማድረግ ተግባር ያለውን የመፍትሄ አማራጭ እና ወሳኝ አስተዋፅኦ አጉልቶ ያሳያል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሶላር ኢነርጂ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን የቦርድ አባል የሆኑት አቶ ግዛቸው ፈሩ በአባዛኛው በኢትዮጵያ ገጠራማ ክፍል የሚኖረው ማህበረሰብ በኤሌክትሪክ ተደራሽ አለመሆኑን ጠቁመው ይህንን ችግር ለመቅረፍ መንግስት ፕሮግራም ቀርጾ እየሰራ መሆኑንና ለዚህ ፕሮግራም ስኬታማነት ትልቁ አማራጭ ደግሞ የሶላር ሀይል ነው ብለዋል፡፡

አክለውም የሶላር አማራጭ የመብራት አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የህብረተሰቡን የኑሮ ደረጃ በማሻሻልና በማዘመን ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወትና በተያዘው ፕሮግራም መሰረትም በሚቀጥሉት ሶስት እና አራት ዓመታት በዘርፉ ከፍተኛ ለውጥ ይመጣል ብለዋል፡፡

Share this Post