አገር አቀፍ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ላይ ውይይት ተካሄደ።

አገር አቀፍ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ላይ ውይይት ተካሄደ።

ሚያዚያ/2016 (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አገር አቀፍ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርን እውን ለማድረግ የሚያስችለውን የአጋር አካላት ውይይት በአዲስ አበባ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አዳራሽ አካሂዷል።

በእለቱ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር አብርሃ አዱኛ የዝዋይ ሻላና አዋሽ ንኡስ ተፋሰስ ላይ እየተሰሩ ያሉ የውሃ ሀብት አስተዳደር ስራዎች ልምድ የምንቀስምበት ፣በርካታ ነገሮችን የምንማርበት፣ አገራዊ ፕሮግራማችን የምናስተዋውቅበት እና ወደፊት በፕሮግራሙ ላይ ያለውን አስተዋጽኦ እንድናውቅ የማድረግ አቅምን ያሳድጋል ብለዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፕሮግራሙን እውን ለማድረግ ወሳኝ ሚና ካላቸው ከፌደራል ጀምሮ በየደረጃው ላሉ ተቋማት እና አጋር ድርጅቶች ስለ ሀገራዊ መርሃ ግብሩ ግንዛቤ እያስጨበጠ ይገኛልም ብለዋል ክቡር ሚ/ዴኤታው።

ውይይቱ የውሃ ሀብታችን ፍትሀዊ፣ ዘለቄታዊና ፈጣን በሆነ መልኩ በማልማት ለማስተዳደር ከአጋር አካላትና ከሚመለከታቸው ጋር በጋራ የምንሰራበትን ሁኔታ ያመቻቻል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በተሰጠው ስልጣን መሰረት የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርን በመንከባከብ፣ ደህንነቱን በማስጠበቅና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ለማስተዳደር በቁርጠኝነት ይሰራል ብለዋል።

ላለፉት ሶስት ቀናት በአውሮፓ ህብረትና በኔዘርላንድ የሚደገፈው ፕሮጀክት ላይ ውይይት ሲደረግ መቆየቱን የጠቀሱት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ከሚመከታቸው አካላት ጋር በመሆን ጽ/ቤቶች በፕሮግራሙ አተገባበር ላይ ያለውን ተሞክሮ በመለየት ለማስፋት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ፕሮግራሙን ውጤታማ ለማድረግ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ቡድን መቋቋሙን የገለጹት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው የመፈጸም አቅም፣ የሰው ሀብት ልማት፣ የህግ ማዕቀፍ፣ የአሰራርና የቴክኖሎጅ ክፍተቶችን በመለየት በየደረጃው ባሉ መዋቅሮች ችግሩን ለመቅረፍ የሚያስችል ውይይት ተደርጓል ብለዋል፡፡

የፕሮግራሙ ዋና አላማም በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቀናጀ ውሃ ሀብት አስተዳደር ስራን ቀስ በቀስ እንዴት ማላመድ እንደሚቻል አነቃቂ ምስሎች፣ በWoord and Daad እንዲሁም በ Wetlands International የተከናወኑ አለም አቀፍ ተሞክሮዎች የፕሮግራሙን የወደፊት ራዕይ የሚያሳዩ እና ጥያቄዎችንም የሚመልሱ እንደሚሆኑ ጠቁመዋል፡፡

በእለቱ በተቀናጀ ውሃ ሀብት አስተዳደር ላይ የአዋሽ ተፋሰስ ምርጥ ተሞክሮ በ Mr. Gerden van Genderen and አቶ አብርሃም ድርባባ እንዲሁም የZSBIB ፕሮጀክት ምርጥ ተሞክሮ በMr. Jeroen Jurriens ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

Share this Post