ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ከአለም ባንክ የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጠና የመሰረተልማት ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ፡፡

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ከአለም ባንክ የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጠና የመሰረተልማት ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ፡፡

መጋቢት 30/2016 ዓ.ም.(ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ ከአለም ባንክ የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጠና የመሰረተልማት ዳይሬክተር Dr. Wendy Hughes ጋር በኢነርጂ ሴክተር ሪፎርም ዙሪያና ሌሎች የኢነርጂ ልማት ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡

ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ የኢነርጂ ሴክተር ሪፎረም ሂደትን አስመልክተው ገለጻ ባደረጉበት ወቅት የኢነርጂ ሴክተር ሪፎረም ፍኖተካርታ ከአመታት በፊት መዘጋጀቱንና በትግበራ ሂደት ላይ መሆኑን ገልጸው፤ የብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም እና የብሔራዊ ኢነርጂ እስትራቴጂን የመከለስ ስራዎች እተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ክቡር ሚነስትር ዴኤታው አክለውም እንደሀገር የኤሌክትሪክ ሽፋን ተደራሽነት ከ52በመቶ ያልዘዘለለ መሆኑን አውስተው፤ የዘርፉ ተግዳሮት የሃይል እጥረት ሳይሆን ብቃት ያለው የሀይል ስርጭትና ማስተላለፊያ መሰረተልማት መዘርጋት ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ክቡር ሚነስትር ዴኤታው ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ፓወር ፑል ዋና ተዋናይ እንደሆነች ገልጸው፤ የምስራቅ አፍሪካ ፓወር ፑል ከደቡብ አፍሪካ ፓወር ፑል ጋር የማስተሳሰር ፍላጎት እንዳለ ተናግረዋል፡፡

Share this Post