የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከአፋር ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ጋር የተጓዳኝ በጀት ውል ስምምነት ተፈራረመ፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከአፋር ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ጋር የተጓዳኝ በጀት (maching fund) ውል ስምምነት ተፈራረመ፡፡ ህዳር 27/2017ዓ.ም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በአፋር ክልል ለሚገነባው የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ የተጓዳኝ በጀት (maching fund) ከ51 ሚሊየን ብር በላይ ከክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ጋር ውል ተፈራርመዋል፡፡ ስምምነቱ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በክቡር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞና በአፋር ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ በአቶ አህመድ ሻሚ በኩል የተካሄደ ሲሆን በክልሉ ለሚገነባው የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ከስራው ተቋራጭ ጋር የውል ስምምነት ከመገባቱ በፊት የውሃ ኢነርጂ ሚኒስቴር ለግንባታው ከሚያወጣው በጀት በተጓዳኝ የክልሉ ውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ ለስራው የሚያስፈልግ በጀት እንዲያቀርብ የሚያስችል ስምምነት ነው፡፡

Share this Post