በሚኒ-ግሪድ ታሪፍ ስሌትና ዲጂታላይዜሽን የፈቃድ አሰጣጥ ሂደቶች ዙሪያ ቴክኒካል ስልጠና መሰጠት ተጀመረ፡፡

በሚኒ-ግሪድ ታሪፍ ስሌትና ዲጂታላይዜሽን የፈቃድ አሰጣጥ ሂደቶች ዙሪያ ቴክኒካል ስልጠና መሰጠት ተጀመረ፡፡

ሚያዚያ 14/2016.ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ ሶላር አሊያንስ ጋር በመተባበር የአነስተኛ ግሪድ የታሪፍ ስሌት ላይ እና ፈቃድ አሰጣጥ ሂደቶችን ዲጂታላይዜሽን ማድረግን በተመለከተ በራዲሰን ብሉ ሆቴል ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡

የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ ሶላር አሊያንስ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ስልጠና በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጅ ዘርፍ አማካሪ አቶ ጎሳየ መንግስቴ በሚኒ-ግሪድ ታሪፍ ስሌት እና ዲጂታላይዜሽን የፍቃድ አሰጣጥ ሂደቶች ዙሪያ ሁለት ወሳኝ ገጽታዎችን፤ ማለትም ለትንንሽ ግሪድ ኦፕሬተሮች የዋጋ መመሪያ እና የመቆጣጠሪያ ሂደቶችን ዲጂታይዜሽን የሚዳስስ መሆኑን ጠቅሰው፤ በገጠር አካባቢዎች ለሚገኙ የማህረሰብ ክፍሎች ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ እድገትን ለማሻሻል እና የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ ሚኒ ግሪድ ላይ ዘላቂ አሠራር እንዲኖራቸው የማድረግ ወሳኝነት አለው ብለዋል፡፡

አቶ ጎሳዬ በማያያዝ ይህ የስልጠና በየክልሎች ውስጥ ያሉ የሚኒ ግሪዶችን ሥራ ቀጣይነት ለማሻሻል አስፈላጊ እውቀት እና ክህሎት እንደሚያስጨብጥና ለህብረተሰቡም ንጹህ ፣ አስተማማኝእና ዘላቂነት ያለው ኃይል ለማግኘት አስተዋጽኦ ያደርጋል ብለዋል፡፡

የፍቃድ ሂደቶች ዲጂታላይዜሽን የሚኒ-ግሪድ ዘርፉን ውጤታማነት በተለያዩ መንገዶች በእጅጉ ሊያሻሽል እንደሚችልና፤ ከእነዚህም መካከል የፍቃድ አሰጣጥ ሂደቱን ማስተካከል፣ የተሻሻለ መረጃ አያያዝ፣ የኤሌክትሮኒክ የክፍያ ስርዓቶች፣ ወቅቱን የጠበቀ ክትትል፣ የተሻሻለ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ይገኙበታል ብለዋል፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ የዓለም አቀፉ ሶላር አሊያንስ በኢትዮጵያ ተግባራዊ ከሚያደርጋቸው ሌሎች የፕሮግራም ድጋፍ መካከል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሶላር ኢነርጂ ልማት ለማፋጠን፣ አስተማማኝና ውጤታማ የሆነ ሚኒ-ግሪድ አስተዳደራዊ ስርዓት ለመፍጠር የሚያስችል የፍቃድ አሰጣጥ አሰራሩን ዲጂታል በማድረግ ለመደገፍና የመስሪያ ቤቱን ተቋማዊ አቅምን በማጎልበት የታሪፍ ስራዎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ የመገምገምና የመወሰን፣ የግል ኢንቨስትመንት ዘርፉን ማበረታታት የሚያስችል መሆኑ ከመድረኩ ተገልጿል፡፡

በስለጠናው ላይ በአነስተኛ ግሪድ የታሪፍ ስሌት እና የፍቃድ ሂደቶች ዲጂታላይዜሽን እና በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የተዘጋጁ ሰነዶች የቀረቡ ሲሆን፤ ከውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል፣ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ከነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን የተውጣጡ ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል፡፡

Share this Post