3ኛው የኢትዮጵያ ውሃና ኢነርጂ ሳምንት ላይ ለተሳተፉ የልማት አጋሮችና የግል ድርጅቶች ዕውቅና ተሰጠ

3ኛው የኢትዮጵያ ውሃና ኢነርጂ ሳምንት ላይ ለተሳተፉ የልማት አጋሮችና የግል ድርጅቶች ዕውቅና ተሰጠ

ጥቅምት 20/2019 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ''ለውሃና ኢነርጂ ዋስትና የተጠበቀለት የወደፊት ሁኔታ ሳይንሳዊ መሰረት ያላቸውን ፖሊሲዎችና አጋርነቶችን ማሳደግ'' በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም ተዘጋጅቶ በነበረው አውደ ርዕይ ላይ አስተዋፅኦ ላበረከቱ፣ በፋይናንስ ላገዙ ተቋማት፣ የልማት አጋሮች እና የግል ድርጅቶች እውቅና በመስጠት ተጠናቀቀ።

አውደ ርዕዩ በውሃውና ኢነርጂው ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለህብረተሰቡ ለማሳየትና ተሞክሮዎችን ለመጋራት ታስቦ የተዘጋጀ ነው ያሉት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የክቡር ሚኒስትር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ማሙሻ ኃይሉ በሳምንቱ ሲካሄዱ የነበሩ የተለያዩ ሁነቶች በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላደረኩ ከ70 በላይ አካላትን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ምስጋናቸውን ገልፀዋል ብለዋል።

በማጠቃለያ መርሃግብሩ ላይ የቀድሞ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሮች ተገኝተው በተቋሙ የነበሩ ስኬቶችን በማጋራታቸው አክብሮታቸውን ያስተላለፉት ክቡር ሚኒስትሩ በዘርፉ ለተመዘገቡ ውጤቶችና ለተደረጉ የልማት ጥረቶችና ለነበራቸው አስተዋፅኦም አድናቆታቸውን ገልፀዋል።

3ኛው የኢትዮጵያ ውሃና ኢነርጂ ሳምንት ላይ ለተሳተፉ የልማት አጋሮች እና የግል ድርጅቶች እንዲሁም ከደቡብ አፍሪካ፣ ከካሜሮን፣ ከኬኒያ፣ ከቻይና፣ ከዴንማርክ፣ ከእስራኤል፣ ከጣልያንና ከኔዘርላንድ ኤምባሲ ለተሳተፉ እንዲሁም ለፕግራሙ ፓናሊስቶች፣ አስተባባሪዎች እና ሁነቱን ለህዝብ ተደራሽ እንዲሆን ላደረጉ የሚዲያ አካላት ክቡር ሚኒስትሩ የምስጋና መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ለተሳተፊዎቹም እውቅና በመስጠት ተጠናቋል።

Share this Post