ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ድንቁ ስዩም ከአለም ባንክ ልዑካን ጋር በኢነርጂ ተደራሽነት ፖርትፎሊዮ ዙሪያ ውይይት አደረጉ

ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ድንቁ ስዩም ከአለም ባንክ ልዑካን ጋር በኢነርጂ ተደራሽነት ፖርትፎሊዮ ዙሪያ ውይይት አደረጉ

ጥቅምት 27/2019 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ.) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ድንቁ ስዩም ከአለም ባንክ ልዑካን ጋር በኢነርጂ ተደራሽነት ፖርትፎሊዮ ማብራሪያ ላይ ውይይት አደረጉ።

የኢነርጂ ተደራሽነት ፖርትፎሊዮ ማብራሪያ /Energy Access Portfolio Briefing/ ላይ ከአለም ባንክ ልዑካን ጋር የኢትዮጵያን የኢነርጂ ተደራሽነት ለማስፋት በተያዙ ዕቅዶች፣ በተከናወኑ ስራዎችና ወደፊት ሊከናወኑ በሚገቡ ተግባራት ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ በከተማና በገጠር የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች፣ የታዳሽ ኃይል ልማት በመጠቀም የኢነርጂ አቅርቦትን ማሳደግ፣ ከኤሌክትሪክ መስመር ውጪ ለሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተስማሚ የኃይል አማራጮችን /Off-grid Solutions/ ማስፋፋት፣ ለኢነርጂ ፕሮጀክቶች የሚያስፈልጉ የፋይናንስ ምንጮችንና የልማት አጋርነትን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አብራርተዋል።

ኢነርጂን ለምርታማነት በመጠቀም የሀገርን ኢኮኖሚ ማሳደግ ይገባል ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በሶስተኛው የብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም /NEP 3.0/ መርሃ ግብር የተያዙ ግቦችና የአፈፃፀም ሂደቶች እንዲተገበር በአለም ባንክ በኩል ሲደረጉ የነበረውን ድጋፍ አድንቀው፤ በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

የአለም ባንክ ኦፕሬሽን ማናጀር ዶ/ር ጁሊያና ቪክቶር በበኩላቸው በኤሌክትሪክ ተደራሽነት ላይ ተቋሙ እየሰራ ያለውን ስራ አድንቀው ይህም ከፍተኛ ኢንቨስትመንት በመሆኑ የሁሉንም ወገን ድጋፍ ስለሚፈልግ ስለሆነ፤ እኛም በሚጨበጥ ውጤት ላይ አተኩረን እየሠራን በመሆኑ ድጋፉን አጠናክረን እንቀጥላለን በማለት ቃል ገብተዋል።

Share this Post