የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት የሕልውና፣ የኢኮኖሚ ፍትሐዊነትና የትውልድ መብት ጉዳይ ነው፡፡
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 16/2019ዓ.ም
የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ፍላጎት ከሀገሪቱ ታሪካዊ ሁኔታ፣ እያደገ ከመጣው የሕዝብ ቁጥርና ከሰፊው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጋር በቀጥታ የተያያዘ የሕልውና፣ የኢኮኖሚ ፍትሐዊነትና የትውልድ መብት ጉዳይ ነው።
የሀገሪቱ የሕዝብ ቁጥር እያደገ መምጣትና የምርት፣ የንግድ፣ የኢንዱስትሪና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች መስፋፋት የባሕር በር ተደራሽነትን ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገትና የወደፊት ብልጽግና ወሳኝ ጉዳይ ያደርጉታል።
ከውሃና ኢነርጂ ዘርፍ አኳያ የባሕር በር ተደራሽነት ለኃይል ትስስር፣ ለኢነርጂ ንግድና ለቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትብብር አዳዲስ ዕድሎችን የሚፈጥር ነው።
የውሃና የኃይል ሀብቶችን በጋራ ማልማትና በተቀናጀ መልኩ መጠቀም ለአገራት የጋራ ብልጽግና፣ ለቀጣናዊ ትስስርና ለዘላቂ ልማት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው።
የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት በሰጥቶ መቀበል፣ በጋራ ጥቅምና በትብብር መርሆች ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ ለጎረቤት ሀገራት የጋራ ልማትና የኢኮኖሚ ትስስር ዕድሎችን የሚያሰፋ ነው። ይህም በቀጣናው የንግድ እንቅስቃሴን ከማሳደግ ባለፈ የትብብርና የመተማመን መሠረትን በማጠናከር ለዘላቂ ሰላም አስተዋጽኦ ያደርጋል።
ኢትዮጵያ የቀይ ባሕርን ሰላምና የባሕር ላይ ንግድ ደኅንነት ለማረጋገጥ ሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን የምትደግፍ ሲሆን፣ የባሕር በር ተደራሽነት ጉዳይ በውይይት፣ በመግባባትና በጋራ ጥቅም መርህ እንዲፈታ ቁርጠኛ ናት።
ይህም ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ብልጽግናና ለቀጣናው የጋራ ልማትና ዘላቂ ሰላም መሠረት ይሆናል።
ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto