የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የጎርፍ አደጋን የመከላከል ስራን በተጠናከረ መንገድ ለመፈጸም ሚያስችል ስልጠና ለባለድርሻ አካላት ተሰጠ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የጎርፍ አደጋን የመከላከል ስራን በተጠናከረ መንገድ ለመፈጸም ሚያስችል ስልጠና ለባለድርሻ አካላት ተሰጠ።

የካቲት /2016 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ)

ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የጎርፍ አደጋ ለመከላከል በተቀረጸ ፕሮጀክት ላይ መሰረት አድርጎ የጎርፍ መከላከል ስራን በተጠናከረ መንገድ ለመፈጸም ሚያስችል ስልጠና ተሰጠ።

የምክክር መድረኩን በንግግር የከፈቱት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴኤታ ማእረግ የክቡር ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ ክቡር አቶ ሞቱማ መቃሳ በሀገራችን የሚከሰቱ የጎርፍ አደጋን ለመከላከል የሚመለከታቸው ፈጻሚ አካላት ጋር ጊዜ ወስዶ በፕሮጀክት አፈጻጸም እና አጠቃላይ ስለፕሮጀክቱ ስልጠና መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ ይህ ስልጠና ተዘጋጅቷል፤ ስለዚህ በሀገራችን የሚስተዋሉ የጎርፍ አደጋ የሚያስከትሉ ጉዳቶቾን ለመቀነስ በተናበበና በተጠናከረ መንገድ መስራት እንደሚያስፈልግና የሀብት አጠቃቀማችንም ውጤትን መሰረት ያደረገ መሆን እንደሚገባው ገልጸዋል።

የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ተመስገን ከተማም አጠቃላይ ፕሮጀክቱ ሰለመጣበት ሂደት ሰፋ ያለ ማብራሪያ አቅርበዋል ። እንዲሁም ከአደጋ ስጋት አስተዳደር ኮሚሽን አቶ ይርጋ እያሱ ተቋሙ ስለሚሰራው ስራ እና ይህንን ፕሮጀክት ለመፈጸም ስላለው ዝግጅት ብሎም ተቋሙ ስላለበት ችግር በጽሁፋቸው አቅርበዋል ።

የኢትዮጲያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲዩትም ስለፕሮጀክቱና ከተቋሙ ስለሚጠበቁ ዝርዝር ጉዳዮች በአቶ ለታ በቀለ ቀርቦ በተሳታፊዎች ጥያቄ፣ ሀሳብ ና አስተያየት ቀርቦ በአቶ ሞቱማ መቃሳና ከጽሁፍ አቅራቢዎች ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቷል።

Share this Post