Energy Access Explore Application ወደ ሥራ ለማስገባት ስልጠና ተሰጠ

በሀገራችን የኢነርጂ ተደራሽነት ሊያመላክት የሚችል Energy Access Explore ወደ ሥራ ለማስገባት የሚያስችል ስልጠና ተሰጠ መተግበሪያው በአፍሪካ ክሊን ኢነርጂ አስተባባሪነት በወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲትዩትንና የተሰራ ሲሆን በኢትዮጵያ ያለውን የኢነርጂ ተደራሽነት ሁኔታ፣ ፍላጎትና የኢነርጂውን ዓይነት በቦታ ለይቶ መረጃውን ለሚፈልጉ ማሳየት ይችላል ተብሏል፡፡ ይህም በኃይል አቅርቦት ዘርፍ መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ ለሚፈልጉ ባለሀብቶች ጠቃሚ መረጃ ያስገኛል፡፡ የስልጠና መርሐ ግብሩን በንግግር ያስጀመሩት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ሱልጣን ወሊ Energy Access Explore ከሀይል ተደራሽነት ጋር በተያያዘ መረጃዎችን ለመንግሥትም ይሁን ለግል ተቋማት በማቅረብ ረገድ ያለውን ክፍተት እንደሚሞላ ገልጸው መተግበሪያውን ያዘጋጀውን ወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲትዩትንና የሥራውን ሂደት ሲያስተባብር የቆየውን የአፍሪካ ክሊን ኢርጂን አመስግነዋል፡፡ የአፍሪካ ክሊን ኢነርጂ-ኢትዮጵያ ኃላፊ አቶ ኬናሳ ዴሬሳ ስልጠናው የተዘጋጀው መተግበሪያውን ሥራ ላይ ለማዋልና ለለመረጃ ፈላጊዎች በዘላቂነት ተገቢውን መረጃ ለማድረስ እንዲቻል ታሳቢ በማደረግ መሆኑን ገልጸው መተግበሪያውን የሠራው የወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲትዩት ቴክኒካው ድጋፍ በማድረግ ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት እንደሚቆይ ተናግረዋል፡፡

Share this Post