የበጋ የአየር ንብረት ግምገማ እና የመጪው በልግ ወቅት የአየር ጠባይ አዝማሚያ ትንበያ ዙሪያ ውይይት ተደረገ፡፡

የበጋ የአየር ንብረት ግምገማ እና የመጪው በልግ ወቅት የአየር ጠባይ አዝማሚያ ትንበያ ዙሪያ ውይይት ተደረገ፡፡ ጥር 2015(አዳማ ) የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት ባዘጋጀዉ የ2015ዓም የበጋ የአየር ንብረት ግምገማ እና የመጪው የበልግ ወቅት የአየር ጠባይ አዝማሚያ ትንበያ ዙሪያ ውይይት ተደረገ፡፡ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ እንደገለጹት የአፍሪካ ቀንድ በተለይ ባለፉት 3 አመታት በጎርፍና በድርቅ በኢትዮጵያ፣ ኬኒያና ጂቡቲ እንዲሁም ሌሎች አጎራባች ሀገሮች በርካታ ማህበረሰቦችን በማፈናቀል ፤ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ላይ የጣለ መሆኑን ገልፀው፤ በሀገራችን ዜጎች በጎርፍ እንደተፈናቀሉ እና በድርቅ በቦረናና በሶማሌ ዜጎች ለጉዳት መዳረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም ስለ አየር ንብረት ሲታሰብ አንዱና ወሳኙ ዜጎች ሳይፈናቀሉ ባሉበት ቦታ ሆነው እንዲቋቋሙ እና ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የመረጃ ስርጭት ትልቁን ሚና እንደሚወስድ ገልጸው ኢኒስቲቲዩቱ በዚህ ረገድ ትልቅ ስራ እየሰራ መሆኑን አስታውሰው፤ በ2015 የበልግ ቅድመ ትንበያ ላይ የሚመለከታቸው አካላት በተለይ ሚዲያዎች ከፍተኛ ድርሻ በመውሰድ በአጭር፤ በመካከለኛ በረጂም ጊዜ ኢኒስቲቲዩቱ የሚሰጣቸውን ቅድመ ትንበያዎች ለዜጎች ተዳራሽ እንዲያደርጉ በማሳሰብ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በመድረኩ የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ ባለፈው የበጋ ወቅት የአየር ጠባይ ግምገማና በሚቀጥለው የበልግ ወቅት በሚጠበቀው የአየር ጠባይ ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

Share this Post