በህ/ተወ/ም/ቤት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በሲዳማ እና ኦሮሚያ ክልል የመስክ ምልከታ አደረጉ፡፡

በሕ/ተወካዮች ም/ቤት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በሲዳማ እና ኦሮሚያ ክልል የመስክ ምልከታ አደረጉ፡፡

ጥር 2015 ዓ/ም የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮችና ቋሚ ኮሚቴው በሲዳማ እና በኦሮሚያ ክልሎች በአማራጭ ኢነርጂ ዘርፍ አዲስ የተገነቡና አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉ የልማት ቦታዎችን ጎብኝተዋል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው በዮዎ ቀበሌ ባደረገው የመስክ ምልከታ በሶላር ሀይል የሚሰራ ከ4400 አባውራ በላይ ተጠቃሚ የሚያደርግ ጥልቅ የመጠጥ የውሀ የጉድጓድ ተመልክተዋል፡፡ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ጥበቡ እንደገለጹት በሶላር ሀይል መካከለኛ ጥልቅ የጉድጓድ ውሀ ከግሪድ ውጭ ላሉ አካባቢዎች የሶላር ሀይልን በመጠቀም የንጹህ መጠጥ ውሀ ማቅረብ እንደሚቻል ማሳያ ነው ያሉት አስተባባሪው በዮዎ ቀበሌ ቤኒ መንደር ተግባራዊ ሲደረግ ከ4400 አባወራ በላይ እና ለ8 ቀበሌዎች ተደራሽ የሚያደርግ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ አያይዘውም ፕሮጀክቱ ያለምንም ችግር ለ30 አመት አገልግሎት መስጠት እንደሚችል ገልጸዋል፡፡ አካባቢው በከርሰ ምድር ውሀ የበለጸገ በመሆኑ ከላይ ጸሀይ ከስር ውሀን በማቀናጀት የኢነርጂ ተጠቃሚ መሆን እንደሚቻልም አስረድተዋል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው ፕሮጀክቱን ትኩረት በመስጠት የተመለከተው ሲሆን ይህ ፕሮጀክት የከርሰ ምድር ውሃን ከጸሀይ ሀይል ጋር በማቀናኘት የተሰራ በመሆኑ በተለይ በከርሰ ምድር ውሃ የበለጸጉ አካባቢዎች ተሞክሮውን በመውሰድ መስራት እንደሚገባቸው የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር አወቀ አምዛዬ ገልጸዋል፡፡ በተያያዘ በሀዋሳ እና ሻሸመኔ ከተማ የተገነቡና ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት የጀመሩ 5 የጋራ መጸዳጃ ቤቶችን የተመለከቱ ሲሆን፤ እነዚህ መጸዳጃ ቤቶች ከአለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ የተሰሩና እንደ ሀገር የሚተገበር ፕሮግራም መሆኑን የከተማ ሳኒቴሽንና መሰረተ ልማት ጥናት ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ዴስክ ሀላፊ አቶ ዳባ ዴሲሳ ገልጸው ፕሮግራሙ አዲስ አበባን ጨምሮ በ23 ከተሞች ተግባራዊ የሚደረግና ለ6 አመት እንደሚቆይ ጠቁመው 533 ሚሊየን ዶላር በጀት የተያዘለትና አሁን ላይ በሀዋሳና በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ላይ ተግባራዊ በማድረግ ለህረተሰቡ መጠጥ ውሀን መስጠት ብቻ ሳይሆን መጸዳጃ ቤቶችን በመገንባት ንጽህናው የተጠበቀ አካባቢን ለመፍጠር እየሰሩ መሆኑን ገልጸው በአጠቃላይ 3.38 ሚሊየን የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል የባዬ ጋዝ ኢነርጂን አስመልክቶ በውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር የብሔራዊ ባዮጋዝ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ተመሰገን ተፈራ እንደገለጹት የባዩ ጋዝና አማራጭ ኢነርጂ ፕሮግራም እ.ኤ.አ በ2008 ዓም የተጀመረ እና በሀገራችን በ8 ክልሎች ተግባራዊ እየተደረገ ያለና 23 ሚሊየን ዩሮ የተበጀተለት መሆኑን ገልጸው፤ በዚህም ለስራው የሚረዳ 41 ሺ ዳጀስተር በሀገሪቱ በማሰራጨት ከጤና፣ ከትምህርት፣ ከግብርና ምርትና ምርታማነት ከማሳደግ፣ ለወጣች የስራ እድልን ከመፍጠር አንጻር ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል ፡፡ ከዚህም ባሻገር ንጹህ ኢነርጂን ለህረተሰቡ ለማዳረስ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ማናጀሩ በዚህ ስራ ላይ ስትሪንግ ኮሚቴ የተቋቋመ እና ከክልል እስከ ወረዳ እየተሰራ በመሆኑ ቋሚ ኮሚቴው በተለይ ለግንባታ ችግር እየፈጠረብን ያለውን የሲሚንቶ ችግር መፍትሄ እንዲሰጡን እንጠብቃለን በማለት ገልጸዋል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው በጉብኝቱ በሀዋሳ እና በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ በሶላር ሀይል ጥልቅ የጉድጓድ ውሀ፣ በGiz ድጋፍ የተተከሉ የሶላር የአትክልት ማቀዝቀዣ፣ የሀይል ቆጣቢ ምድጃ አምራች ማህበር፣ ባዮጋዝ ተጠቃሚዎችን እና የጋራ መፀዳጃ ቤቶችን መጎብኘት ችለዋል፡፡

Share this Post