ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከአማራ ብሔራዊ ክልል የክብር ሽልማት ተበረከተለት፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሠራተኞች ለሕልውና ዘመቻው ስኬታማነት ላበረከቱት ዘመን የማይሽረው አስተዋጽኦ ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከአማራ ብሔራዊ ክልል የክብር ሽልማት ተበረከተለት፡፡ የክብር ሽልማቱን ክቡር ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እጅ ተቀብለዋል፡፡ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ቀደም ብሎም በመከላከያ ሚኒስቴር 6ኛ ዕዝ ጠቅላይ መመሪያ በዘመቻው ለነበረው አስተዋጽኦ የዋንጫና የሰርተፍኬት ሽልማት አግኝቷል፡፡

Share this Post