የዓለም የውሃ ቀን በሴኔጋል ዳካር ተከበረ

የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነትን ታሳቢ ያደረገ የውሃ ሀብት አጠቃቀም መከተል እንደሚገባ ተገለጠ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በሴኔጋል ዳካር በመካሄድ ላይ ባለው የዓለም የውሃ ፎረም ጋር ተያይዞ በተካሄደ የአፍሪካ የውሃ ሚኒስትሮች ምክር ቤት (AMCOW) 20ኛ የምስረታ ጉባዔ ላይ ምስራቅ አፍሪካን በመወከል ባደረጉት ንግግር በውሃ ሀብት አጠቃቀማችን ላይ የአየርን ንብረት ለውጥ ተጋላጭነትን ታሳቢ ያደረገ አጠቃቀም መከተል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ውሃ ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም፣ የዝናብ ውሃና ማሰባሰብ( ማቆር) እና የከርሰ ምድር ውሃ ማውጣትና መጠቀም ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡ ሚኒስትሩ በ9ኛው የዓለም የውሃ ፎረምም ላይ እየተሳተፉ ሲሆን በተመሳሳይ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በአፍሪካ የውሃ ሚኒትሮች ምክር ቤት ምክትል ሰብሰቢ ናቸው፡፡

Share this Post